https://t.me/ethio_telecom/6335
T.ME
Ethio telecom ኩባንያችን በ2016 በጀት ዓመት የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽና አካታች በማድረግ የማህበረሰባችን ቁልፍ ችግሮች የሚፈቱ እንዲሁም የሀገራችንን ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያፋጥኑ በርካታ ተግባራት በማከናወን ስኬቶችን ተጎናጽፏል፡፡
በበጀት ዓመቱ የቴሌብር ደንበኞቻችንን ብዛት 47.55 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዳችንን 107.8% ያሳካን ሲሆን ኩባንያችን ከዳሸን ባንክ እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር እያቀረበ በሚገኘው የማይክሮ ብድር፣ የማይክሮ ቁጠባ እና ኦቨር ድራፍት አገልግሎቶች ለ2.9 ሚሊየን ደንበኞች 9.35 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አቅርቧል፡፡
በተጨማሪም በቴሌብር አማካይነት 1.3 ሚሊየን ደንበኞች 9.72 ቢሊዮን ብር መቆጠብ የቻሉ ሲሆን አገልግሎቱ ከጀመረበት ከነሐሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ 5.3 ሚሊየን ደንበኞች 12.88 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት እንዲሁም 2.1 ሚሊየን ደንበኞች ደግሞ 13.35 ቢሊዮን ብር መቆጠብ ችለዋል፡፡
በቴሌብር የገንዘብ ዝውውርን ዲጂታላይዝ በማድረግ በበጀት አመቱ 1.81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የተዘዋወረ ሲሆን አገልግሎቱ ከተጀመረ ጀምሮ በኢኮኖሚው ውስጥ 2.55 ትሪሊየን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡
ውድ የኩባንያችን ቤተሰቦች፣ ክቡራን ደንበኞቻችን እና የሥራ አጋሮቻችን በቴሌብር የስኬት ጉዞ አብሮነታችሁ ስላልተለየን ከልብ እናመሰግናለን!
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3VWyKnZ ይጠቀሙ፡፡
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_እውን_በማድረግ_ላይ_እውን_በማድረግ_ላይ
#telebirr #Ethiotelecom #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #ECA #HOPR #HoF