በሀገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ኢትዮጲያ ውስጥ ተቀምጠው ውጭ ሀገር የሚገኙ የኦንላይን ስራዎችን ይሰራሉ ። አብዛኛዎቹ የኦንላይን ስራዎች የሚከፍሉት በ Pay Pal ነው። ከፔይፓል ገንዘብ አውጥቶ ወደ ኢትዮጲያ ለማስገባት ምንም አይነት አመቺ ሁኔታ የለም ። ይህ ከውጪ የሚመጣ ገንዘብ ሀገራችን ውስጥ ቢገባ ሀገሪቷን የውጪ ምንዛሬ እጥረቷን ይቀርፋል። ስለዚህ ቴሌብር ከውጭ ሀገር የፋይናንስ ድርጅቶች ጋር ራሱን በማስተሳሰር በቀጥታ የሰራነውን ገንዘብ የምንቀበልበትን ሲስተም ቢያዘጋጅ ለሀገራችንም አንድ እርምጃ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ምን ታስባላችሁ ?