ኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ ዝርጋታችሁ የተጠና ነዉ ወይ? Digital Divideን እናንተ ራሳችሁ አገሪቱ ዉስጥ እንዲስፋፋ መንገድ እየጠረጋችሁ መሆኑን እንዴት አይገባችሁም? Addis Ababa, Adama or ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ወደ 4/5G Upgrade ቢሆኑ ሌሎች ትናንሽ ከተሞች መታየት የለባቸዉም ወይ? ወይስ ኢትዮ ቴሌኮም ስራዉ ለአዲስ አበባ እና ለአዲስ አበባ ቅርብ ከተሞች ነዉ?
አንዳንዴ ክፍለ አገር ቤተሰብ ጋር ስንሄድ የሚናየዉ ነገር አገሪቱ ዉስጥ ቴሌኮም ድርጅት አለ ወይ ያስብላል። ትንሽ ገባ ያለ ቤት ዉስጥ የኢንቴርኔት ይቅርና የስልክ ኔትወርክ ማይሰራበት ቦታዎች እያሉ ፣ ኔትወርክ ፍለጋ ሰዎች ተራራ ላይ እስኪወጡ ስቸገሩ እያየን ፣ ሰዎች ኔትወርክ ማለትም #ለስልክ የሌለዉ ኔትወርክ #ለእንቴርነት ከየት ይመጣል በሚል ከሌላው ርቆ (Digital Divide) ወደ ኋላ መቅረታቸዉን እያየን ቢናወራ ምንም መልስ የለም። ክፍለ አገር ያሉ ታወሮችን ወርዳችሁ ለምን አትታዩም? ለምን ወረድ ብላችሁ ችግሩን አይታችሁ ለመስራት አትሞክሩም። ቴክኖሎጂ ሁሉንም ያቀፈ መሆን አለበት እንጂ ቀድሞዉንም access ያለዉን ይዛችሁ ወደፊት ከሄዳችሁ ላልደረሰዉ እና ከቴክኖሎጂዉ በጣም ለራቀዉ ማን አለ?
የኢንቴርነት ችግር ሙሉ #የአገሪቱ ገጠር አከባቢዎች ችግር ነዉ። ገጠር ህብረተሰብ የናንተን 5G/4G ኔትወርክ አይፈልግም። Stable የሆነ 2G ኔትወርክ #ካላስቸገርናችሁ ደግሞ የምሰራልን 3G ኔትወርክ እንፈልጋለን። ጥሩ ስማርት ስልክ ይዘን 3G/4G ስለማይሰራ ወደ 2G ቀይረን እሱንም በስቃይ ነዉ። ኢትዮ ቴሌኮም መስራት ካለበት ሁሉንም እኩል ወደ ቴክኖሎጂ ማምጣት አለበት። 5G ለከተማዉ ኖሮ ማለትም 2G/3G በአገሪቱ ሳያዳርሱ 5G ጀምረናል ማለት እበደት ነዉ። የአገር ተቋም እስከሆነ ድረስ ሌሎችን ማሳተፍ እና ቢያንስ Stable የሆነ 3G ኔትወርክ ከሌለ የ5G ኔትወርክ ተዳራሽነቱ አይታይም። በእርግጥ ፌዴራል ከተማን ከክልል እና ከዞን ከተማ ጋር ለማነጻፀር ሳይሆን ፈደራል ከተማ #ሁለት ሶስት እርምጃ ከፍ ብል የክልል እና የዞን ከተሞችም ቢያንስ ከነበሩበት የኔትወርክ ችግር በአንድ እርምጃ መዉጣት አለባቸዉ።