እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይን ዕውን ለማድረግ እና በ128 ዓመታት በአብሮነት ጉዟችን ስናደርገው እንደነበረው ሁሉ ህዝባችንን የወቅቱን ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተቋዳሽ ለማድረግ የመጨረሻውን የ5ኛ ትውልድ ኔትወርክ (5G) በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በሙከራ ደረጃ አገልግሎቱን ማስጀመራችንን ስንገልጽ በደስታ ነው፡፡
ይህ የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ወሳኝ ተልዕኮ ላላቸው (Mission Critical) እና በተመሳሳይ ወቅት መከናወን የሚፈልጉ አገልግሎቶችን (real time) ለአብነትም የማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ግብርና፣ ህክምና፣ ለመሳሰሉ ኢንዱስትሪዎች እጅግ የላቀ ፋይዳ ያለው እና Internet of Things የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎች በተግባር እውን እንዲሆኑ የሚያስችል አስተማማኝና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ 
አገልግሎቱ የአዳማ ከተማን ስማርት ሲቲ ከማድረግ አኳያ የተያዘውን እቅድ በማሳካት የከተማዋን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በስማርት ቴክኖሎጂ በማሳለጥ አይነተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
በቀጣይም ኩባንያችን የቴሌኮም ስነ-ምህዳሩን የእድገት አዝማሚያ እና አስቻይ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ማስፋፊያዎችን በማከናወን በሌሎች የክልል ከተሞች አገልግሎቱን የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡ bit.ly/3U0aFKY
#ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ