🤴 ኢትዮጵያ በሚሊየኖች የሚቆጠር ተምሮ የተቀመጠ ስራ አጥ ወጣት አላት። በዚህ ዘመን ይህ ሀይል ከሃገሩ ሳይወጣ ውጭ ተቀጥሮ ወይም በተለያዩ የድጅታል ማርኬቲንግ፣ Freelancingና ሌሎችም አለማቀፍ ስራወች ተሰማርቶ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማስገባት ራሱንም ቤተሰቡንም መርዳት ሃገራችንንም ከሌሎች ሀገራት ተወዳዳሪ ማድርግ ይችላል።
ይሄን ለማድረግ ኢትዮጵያውያን እንደ ፔይፓልና ማስተር ካርድ አለማቀፍ የክፍያ አማራጭ የላቸውም ። ኬንያን ጨምሮ በርካታ አፍሪካውያን እነዚህ አማራጮች አሏቸው።
ኬንያን እንደ ምሳሌ ብንወስድ ለዚህ ይረዳ ዘንድ ሳፋሪ ኮም ከፔይፓል ጋር ህጋዊ ስምምነትበማድርረግ አንድ ኬንያዊ በሳፋሪ ኮም ሲም ፔይፓል ሲከፍት ቬሪፋይ ይሆንለታል። ይሄን አገልግሎት ለኢትዮጵያውያን ግን እስካሁን አልፈቀደም።
ቴሌኮም ከውስጥም ሆነ ከውጭ ባንኮች ጋር ስምምነት በማድረግ በቴሌኮም ሲም ካርድ ፔይፓል ቬሪፋይ የሚሆንበት መንገድ ቢፈጠር። ቴሌኮምም የውጭ ምንዛሬ ያገኛል የበርካታ ወጣቶችም ሂወት ይቀየራል ባይ ነኝ። አመሰግናለሁ።👨🎓